Home Blog Car News Toyota አዲስ የሃይል ማመንጫ ሲስተም ከፈተ
Toyota አዲስ የሃይል ማመንጫ ሲስተም ከፈተ

Toyota አዲስ የሃይል ማመንጫ ሲስተም ከፈተ

Toyota ከFuelCell energy ከተባለ ካምፓኒ ጋር በመሆን በCalifornia ግዛት Long Beach ወደብ ላይ የገነባውን የሃይል ማመንጫ እያስመረቀ ነው። የሃይል ማመንጫውን “Tri-gen” ተብሎ የተሰየመ ሲሆን 3 የተለያዩ ምርቶችን ያመርታል።
ታዳሽ የኤሌክትሪክ ሃይል፣ ሃይድሮጅን፣እና የመገልገያ ውሃ።

ሲስተሙ የተገነባው ወደቡ ላይ የToyotaን የሎጂስቲክ ስራዎች እንዲያግዝ ሲሆን ወደቡ በአመት 200,000 Toyota እና Lexus መኪኖችን ያስተናግዳል።
የሃይል ማመንጫው Biogas(ባዮ ጋዝ)ን በመጠቀም በቀን 2.3 megawatts ታዳሽ የኤሌክትሪክ ሃይል፣ እስከ 1,200 kg ሃይድሮጅን፣ እና 5,300 ሊትር የመገልገያ ውሃ ያመርታል።

Toyota አዲስ የሃይል ማመንጫ ሲስተም ከፈተ
Toyota አዲስ የሃይል ማመንጫ ሲስተም ከፈተ

ሃይድሮጅኑን ወደ ወደቡ የሚመጡ እንደ Toyota Mirai ያሉ የሃይድሮጅን መኪኖችን እና ወደቡ ላይ ለሚሰሩ የToyota class 8 የሃይድሮጅን የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለመሙላት ሲጠቀመው ውሃውን ደግሞ ወደ ወደቡ በመርከብ ተጭነው የመጡት መኪኖች ለሽያጭ ከመቅረባቸው በፊት ይታጠቡበታል።

Toyota እንዳለው አዲሱ Tri-gen ሲስተሙ ወደ ከባቢ አየር ይለቀቅ የነበረውን 9,000 ቶን C02 ያስቀራል።

#Toyota#Tri-gen

Add comment

Subscribe to
our newsletter!
Subscribe to
our newsletter!

Stay connected

Subscribe to
our newsletter!

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing. Ut eleifend scelerisque nisi mauris
©2024 Ethiocar - Place to Buy, Sell or Rent Your Car in Ethiopia