Home Blog Car News ብዙ የመኪና አምራቾች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ከነበራቸው እቅድ እያፈገፈጉ ነው
ብዙ የመኪና አምራቾች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ከነበራቸው እቅድ እያፈገፈጉ ነው

ብዙ የመኪና አምራቾች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ከነበራቸው እቅድ እያፈገፈጉ ነው

መኪና
መኪና

ብዙ የመኪና አምራቾች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ከነበራቸው እቅድ እያፈገፈጉ ነው። ብዙ የመኪና አምራቾች የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምረት የነበራቸው እቅድ ላይ በጣም ጥመኞች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከዛ እቅድ ወደ ኋላ ብሎዋል። ይህ ማለትም ይበልጥ ሃይብሪድ እና ሌሎች የሃይል አምራቾጮችን የምጠቀሙ መኪኖች ላይ ትኩረታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። የMercedeሱ CEO አንዳለው ሙሉ በሙሉ የካርበን ልቀት ወደሌላቸው ተሽከርካሪዎች የሚደረገው ለውጥ ከተጠበቀው በላይ ጊዜ የሚወስድ ይሆናል። እናም የሃይብሪድ መኪኖች ላይ ፍላጎት እስካለ ድረስ እስከ 2030 ድረስ የምናመርታቸው ይሆናል። የVolkswagenኑ CEO ደግሞ የፕለጊን ሃይብሪድ ቴክኖሎጂ ወደ ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ ወደ ሆኑ ተሽከርካሪዎች የምንሻገርበት ድልድይ ነው። እናም የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ፍላጎት በመገዛቀዙ Volkswagen ዋገን ይሄን መሻገሪያ የሆነ ቴክኖሎጂ መጠቀም ግድ ብሎታል ብለውዋል። ይሄ በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ፍላጎት መገዛቀዝ ሰፊው ህዝብ የሚጠቀማቸው ተሽከርካሪውች ላይ ብቻ አይደለም። ቅንጡ እና በጣም ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ Rimac እንደተናገረው የሃይፐር መኪና ገዢዎች ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ የሆኑ መኪኖችን እየፈለጉ ይደለም። በዚህ ምክንያት ምን አልባት አሁንም ብዙ በፒስተን ሃይል የሚሰሩ እና ትላልቅ አቅም ያላቸው ኢንጅኖች የያዙ Super Carዎችን ገበያው ላይ ተመልሰው ልንመለከት እንችላለን።

Subscribe to
our newsletter!
Subscribe to
our newsletter!

Stay connected

Subscribe to
our newsletter!

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing. Ut eleifend scelerisque nisi mauris
©2024 Ethiocar - Place to Buy, Sell or Rent Your Car in Ethiopia